Skip to main content
x

እስኪ እንጠያየቅ!

በደርግ ጊዜ ካሳሁን ገርማሞ የሚባል ሰው በፖሊስ ፕሮግራም ውስጥ ‹‹ተጠየቅ!!›› ይል ነበር በግጥም፡፡ ተጠየቅ በቀድሞው የሙግትና የክርክር ሥርዓት ከሳሽ ወይም ጠያቂ ክሱንና የክሱን ምክንያት በዳኛ ፊት ይዘራና ተከሳሹን ወይም ተጠያቂውን፣ ክስህን ስማና በል መልስህን ስጥ ብሎ የሚያስገድድበት ወግ ማዕረግ ያለው ጥሪና ጩኸት ነበር፡፡

ኧረ ምን ይሻለናል?

ፖለቲካና ኢኮኖሚ፣ ዴሞክራሲና ልማት የማይደራረሱ ነገሮች አይደሉም፡፡ ፖለቲካ ወደ ኢኮኖሚነት ይተረጎማል፡፡ ኢኮኖሚም ይቦተለካል፡፡ ልማቱን እንቅ ገተር የሚያደርገው፣ ሲመቸውም መላወስና መንቀሳቀስ የሚያስችለው፣ አደገ ተመነደገ የሚያስብለው ከዚህ በላይ መስፋፋትና መገስገሱን የሚጠናወተው ፖለቲካው ነው፡፡

የትምክህትና የጥበት ልብ አውልቅ ፕሮፓጋንዳ

በተራው ሰው ደረጃም ሆነ በኢሕአዴግ ግንባርና መንግሥት ዘንድ የሚነፍሰው የትምክህትና የጥበት አጠቃቀም፣ በአንድ ፈርጁ የህሊና ድህነትን ለአመል የመቀነስ ጥቅም እንኳ መስጠት ያልቻለ፣ ግልብ፣ ከግልብም ዲዳ ሆኗል፡፡ በሌላ ፈርጁ ደግሞ ማኅበረሰባዊ ግንኙነትን ለማቀራረብም ሆነ ችግሮችን ለመፍታት ከማገዝ ፈንታ እየጓጎጠ የሚያቆስል ጨፍራራ ነገር ሆኗል፡፡

የነባር አመራሮች መልቀቅ ለምን ያስደነግጠናል?

የአምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የእስካሁኑ የሁለት ዓመት የሥራ ዘመን አገርን ጤና የነሱ ችግሮች፣ ተቃውሞዎችና ግጭቶት ታይተው በማይታወቁበት ዓይነትና ግዝፈት የተመዘገቡበት ወቅት ነበር፡፡ የ2007 ምርጫ ያቋቋመው አምስተኛው ምክር ቤት የጀመረውም በአፈ ጉባዔው የመሰናበቻና ሥራ የመልቀቅ ልዩ ልዩ ትርጉም ሥጋትና ግንዛቤ ባገኘ ዜና ታጅቦ ነው፡፡

አምባገነንነትን የሚጠቅሙ ዴሞክራሲን የሚደፈጥጡ ችግሮች

‹‹ዘላቂ ሰላም ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ›› በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ከሠፈሩት ዓላማዎችና እምነቶች መካከል የመጀመርያዎቹ ናቸው፡፡ በዚህ ሕገ መንግሥት መሠረትም ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሕግ ከተቋቋመ 22 ዓመት አልፏል፡፡

ማንነትና የማንነት ቀውስ

እከሌ ከእከሌ ተወለደ፣ እሱ ደግሞ ከእከሌ እንቶኔን ወለደ፣ በማለት በዝርያ ሰንሰለት የምናየው ሰው ከቤተሰብ አንስቶ ተዛምዶው በጎሳ፣ በነገድ፣ ወዘተ እየሰፋና እየተወሳሰበ በሄደ ማኅበራዊ ዳንቴል የተያያዘ፣ ህልውናውም በዳንቴሉ ቅለትና ውስብስቦሽ የሚመራ ማኅበራዊ ፍጡር (ሶሻል ኦርጋኒዝም) ነው፡፡

የፌዴራል ሥርዓቱ ነው ችግራችን ወይስ እኛ ነን

ችግሮቹ? በገነት ዓለሙ “ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ” የተሰኘችው ኢትዮጵያ ነፃ የሆኑ የተለያዩ አገሮች የኅብረት አገር ለመሆን የመፈለግን ጉዳይ በየአገራቸው ሕዝብ ካስወሰኑ በኋላ ለጋራ ጉባዔ የየአገር ተወካዮቻቸውን ልከው ያቋቋሟት አገር ሳትሆን፣ ፊትም የነበረች ግን በሕገ መንግሥት ጉባዔ ነባር የግንኙነትና የአወቃቀር መሠረቷን ቀይራ የቀጠለች አገር ነች፡፡

ሕዝብ ቆጠራውና ሕገ መንግሥቱ

ከአሥር ቀናት አሰልቺ ንዝንዝና ጭቅጭቅ የበዛበት የአዲስ ዓመት ረዥም ‹‹ሽግግር›› በኋላ እነሆ 2010 ዓ.ም. ውስጥ ገብተናል፡፡ የአዲሱን የ2010 ዓ.ም. መዳረሻ ሁለት ሳምንታት የንዝንዝ ጊዜ ያደገው ባለፈው ሳምንት እንዳመላከትኩት፣ ሕዝባዊ በዓላትን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀሚያ የማድረግ ያልተላቀቀን ክፉ ልምድ ነው፡፡ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነው፡፡ የመንግሥት ያለስፍራውና ያለቦታው መግባት ነው፡፡

በዓላት የሕዝብ ናቸው

አገራችን የምታከብራቸው የሕዝብ በዓላት በሕግ የታወጁና በዓለምም የታወቁ ናቸው፡፡ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የግል ድርጅቶችና የንግድ ሱቆች፣ ባንኮችም ጭምር ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ የሚሆኑበት በመሆኑ በተለይ በውጭ ታዋቂ ያደርጋቸዋል፡፡