Skip to main content
x

ከትርፍ በላይ ለዕድገት እናስብ!

በአክሲዮን ተደራጅተው ከተቋቋሙ ኩባንያዎች ውስጥ በውጤታማነታቸው የፋይናንስ ተቋማትን የሚስተካከላቸው መጥቀስ ይከብዳል፡፡ ሌሎችም አክሲዮን ኩባንያዎች እንደ ባንኮች በሆኑ፣ ባተረፉ፣ ትርፍ ባከፋፈሉ ያስብላል፡፡ እነዚህን  ኩባንያዎችን ለመፍጠር ገንዘባቸውን አዋጥተው እዚህ ደረጃ ላደረሷቸው ባለአክሲዮኖች ምሥጋና ይገባቸውና የፋይናንስ ተቋማት ሀብት በቢሊዮኖች የሚቆጠርበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደንበኞችንም አፍርተዋል፡፡

ግልብ ገበያ

በአንድ ሳምንት ውስጥ ሦስት ገጠመኞች አስተናግጃለሁ፡፡ ገጠመኝ አንድ! በአውሮፓውያን አቆጣጠር ተሠልታ፣ የመንግሥት ታክስና ሌሎች ክፍያዎች ተቀናንሰውላት ከምትደርሰኝ ደመወዜ አስቤዛ ለመግዛት ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. (ኦክቶበር 29) በከተማችን ከሚታወቁ ሱፐር ማርኬቶች ወደ አንዱ ጎራ አልኩ፡፡ የምፈልጋቸውን ዕቃ መራርጬ ወደ ገንዘብ ተቀባይዋ አመራሁ፡፡

ባለታርጋ ሕገወጦች

በግብይት ሥርዓታችን ውስጥ በርካታ ግራ የሚያጋቡ ጉዳዮች ይስተዋላሉ፡፡ በርካታ የተምታቱ አሠራሮችም አብረውን ይኖራሉ፡፡ ሕጋዊና ሕገወጥ ድርጊቶች ሲደበላለቁ እንታዘባለን፡፡ በሕጋዊ መንገድ የሚሠራው የልፋቱን ያህል ማግኘት ሲሳነው፣ አየር በአየር የሚነግደው ማማ ላይ ተቀምጦ እንዳሻው ሲሆን መመልከት አዲስ ነገር አይደለም፡፡

ከዛቻ ይልቅ ተግባር ይቅደም!

የምንዛሪ ለውጡ ይፋ ሲደረግ ሁሉም ሰው ሊከሰት ስለሚችለው የሸቀጦችና የአገልግሎት ዋጋ ጭማሪ የአቅሙን ሲተነብይ፣ ሥጋቱን ሲገልጽ ከርሟል፡፡ በምንዛሪ ለውጡ ማግሥት በዋጋ ግሽበት ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ አነስተኛ ነው ተብሎ ነበር፡፡  ያየነው ግን የተገላቢጦሹን ነው፡፡ የምንዛሪ ለወጡ ወሬ በተሰማ ቅጽበት ገበያው ተለወጠ፡፡ የዕቃዎች ዋጋ ናረ፡፡

ያጣ የነጣው የስኳር ፈላጊ ድምፅ!

ዛሬም ስለስኳር እጥረት ልናወራ ነው፡፡ የስኳር ገበያ መላ ቅጡን እያጣ ነው፡፡ የመፍትሔ ያለ ያልተባለበት ጊዜ ግን የለም፡፡ ዛሬም ችግሩ ብሶበታልና የመፍትሔ ያለ የሚል ድምፅ ማሰማት ተገቢ ነው፡፡ ስኳር የተረጋጋ ገበያ ኖሮት ሸማቹ ያለ አቅርቦትና ያለ ዋጋ ችግር የተገበያየበትን ወቅት ማሰብ ከባድ እየሆነ ነው፡፡

ቅድመ ክፍያ ካርዶችን ከማተም የተሻሉ አማራጮችን የዘነጋው ቴሌ

ከሰሞኑ የሞባይል ስልክ የቅድመ ክፍያ ካርዶች ከገበያው በመጥፋታቸው በየሚዲያው፣ ‹‹ኧረ የካርድ ያለህ›› ሲባል ከርሟል፡፡ እየተነሳ ለሚገኘው እሮሮ ምላሽ መስጠት የሚጠበቅበት ኢትዮ ቴሌኮም እንደ ካርዶቹ ሁሉ ድምፁን አጥፍቶ ቢከርምም፣ ካርድ የጠፋበትን ምክንያት አሳውቋል፡፡

ለአከራይ ተከራይ ዕፎይታን የሚያሰፍን ሕግ ይውጣ! 

በ2009 በጀት ዓመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ አዋጆችን አፅድቋል፡፡ እንደሚፀድቁ የሚጠበቁም ነበሩ፡፡ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረቡ አዳዲስ ሕጎች እንደነበሩም እናስታውሳለን፡፡ ማሻሻያ ያስፈልጋቸዋል የተባሉ ሕጎችም በይደር ታልፈዋል፡፡

የጥበብ ሥራዎችና ዝብርቅርቁ የግብይት መንገድ

ዓውደ ዓመት ሊመጣ ነው ሲባል የበግ፣ የፍየል፣ የቅቤ፣ የዶሮና የእንቁላል ገበያ ይጦፋል፡፡ የአልባሳት መደብሮች ገበያ ይሞቃል፡፡ ሌላው ቀርቶ የቤት ዕቃዎችን ሁሉ የሚሸጡ ድርጅቶች የበዓል ሰሞን ገበያቸው ይደራል፡፡ ይህ የተለመደ ነው፡፡ አዳዲስ የሙዚቃ ካሴቶችና ሲዲዎችም እንደልብ የሚሸመቱበት ወቅት ቢኖር የዓውደ ዓመት ወቅት ነው፡፡

ለተማሪዎች የሚቀርበው ትራንስፖርት ይሻሻል!

አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር የዕረፍቱ ወራት ተገባደው አዲስ የትምህርት ዘመን ይጀመራል፡፡ ከሕፃናት መዋያ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ባሉት ዕርከኖች ትምርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ያቀናሉ፡፡ በዚህ ሳምንት መደበኛ ትምህርት የጀመሩ ትምህርት ቤቶች ቢኖሩም አብዛኞቹ ግን ገና ናቸው፡፡