Skip to main content
x

ሕዝብን እያጋጩ አገርን ማተራመስ በታሪክ ያስጠይቃል!

አገርን ከቀውስ ወደ ቀውስ በማሸጋገር ትርምስ መፍጠር አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ በዜጎች ውድ ሕይወት ላይ መቆመር ያሳዝናል፡፡ የኢትዮጵያዊነት የጋራ መገለጫ የሆኑት ጨዋነት፣ አስተዋይነትና አርቆ አሳቢነት ወደ ጎን እየተገፉ ግንፍልተኝነትና ግትርነት እየገነኑ ነው፡፡ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ደም አፋሳሽ ግጭት በተቻለ መጠን በፍጥነት ካልቆመ፣ ሕዝብን ለዕልቂት አገርን ደግሞ ለማያባራ ጦርነት ይዳርጋል፡፡

የከፍታው ዘመን ዕውን መሆን የሚችለው በኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴቶች ላይ ብቻ ነው!

በአዲሱ ዓመት ከፀብና ከጥላቻ የፀዳች ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር ማለት አለብን፡፡ ይህ የመልካም ምኞት መግለጫ አገራቸውን የሚወዱ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ይሆን ዘንድ በብሩህ ተስፋ መነጋገር ይገባል፡

አስመሳዮች በተሰባሰቡበት ከመርህ ይልቅ ገጠመኝ ይበዛል!

አስመሳይነት የአድርባዮች መገለጫ ነው፡፡ በዚህ ድርጊት የሚታወቁ ሰዎች ደግሞ በሞራልና ሥነ ምግባር ዝቅጠት፣ በራስ ወዳድነት፣ በማይገባ ጥቅም ፈላጊነት፣ በዓላማ ቢስነት፣ በብቃት የለሽነትና በሕገወጥነት ተወዳዳሪ የሌላቸው ናቸው፡፡

ሙስና የዝቅጠት መገለጫ ነው!

ሙስና ሌብነት ነው፡፡ ሌብነት ደግሞ ሥነ ምግባር የጎደላቸው የዘቀጡ ሰዎች ድርጊት ነው፡፡ ከግለሰብ ጀምሮ በቡድን የሚካሄድ ሙስና ታማኝነት በሌላቸውና ሥነ ምግባር አልባ በሆኑ ሰዎች የሚፈጸም በመሆኑ፣ በጤናማ ማኅበረሰብ ዘንድ የተናቀ ነው፡፡