Skip to main content
x

የፌዴራል መንግሥቱ ፈተናዎች

‹‹እኛ አጥብበን በመንደር ታጥረን የምናስብ ሰዎች አይደለንም፡፡ ለመላው የአገራችን ሕዝቦች ብልጽግናና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የምናስብ ሰዎች ነን፡፡ የአገራችንን ዕድገት ለማፋጠን የእኛ ሚና ወሳኝ እንደሆነ በአግባቡ እንገነዘባለን፡፡ ከጥልቅ ተሃድሶው መጀመር ወዲህ ከመሬት፣ ከማዕድን፣ ከኮንትሮባንድና ከመሳሰሉት ጉዳዮች ጋር ተያይዘው በሚስተዋሉ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባራት ላይ ዕርምጃ መውሰድ ጀምረናል፡፡

‹‹በኢትዮጵያ ለሚታየው የፖለቲካ ውጥረት አስፈላጊውን መፍትሔ ለማምጣት እንተባበራለን››

የአሜሪካ ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ በኢትዮጵያ የሚታየውን የፖለቲካ ውጥረት ለመቅረፍ አስፈላጊ የሚሆነውን መፍትሔ ለማምጣት እንደሚረባረቡ፣ በአሜሪካ ሴኔት ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሴናተር ጄምስ ኢንሆፍ አስታወቁ፡፡

የብሔር ብሔረሰቦችን ተዋጽኦ በፌዴራል ተቋማት ለማረጋገጥ ትኩረት የሰጠ የሠራተኞች አዋጅ ቀረበ

በመንግሥት ውሳኔ ሠራተኞች ከክልል ተዘዋውረው እንዲደለደሉ ይደረጋል ተቀጣሪዎች ለሕገ መንግሥቱ ታማኝነታቸውን በቃለ መሃላ እንዲያረጋግጡ ይጠየቃሉ የአገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦችን ተዋጽኦ በፌዴራል የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ለማረጋገጥ ዓብይ ትኩረት የሰጠ የፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

ክልሎችን ከአጎራባች ክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች የሚያቀናጅ አገር አቀፍ የከተማ ፕላን ሊዘጋጅ ነው

የአዲስ አበባና የአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን በገጠመው ተቃውሞ ከተሰረዘ በኋላ፣ የፌዴራል መንግሥት በመላ አገሪቱ የተቀናጀ የከተማ ፕላን ለመፍጠር ያረቀቀው አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

በኦሮሚያ ለሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው ተቃውሞ ረግቧል

በኦሮሚያ ክልል ተደርገው በነበሩ የተቃውሞ ሠልፎች የስምንት ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ ከ30 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ፣ መረጋጋት ተፈጥሯል፡፡ ረቡዕ ጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ከአምቦ ጀምሮ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተስፋፍቶ የነበረው የተቃውሞ ሠልፍ መነሻ ምክንያቱ ሰንቀሌ የሚገኘው የአምቦ የማዕድን ውኃ ወደ ትግራይ ክልል ሊሄድ ነው በሚል እንደሆነ መነገሩ ይታወሳል፡፡

የኢጋድ አባል አገሮች የደቡብ ሱዳን ተገዳዳሪ ኃይሎችን ለማስታረቅ እየጣሩ ነው

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና ዋነኛ ተቃዋሚያቸው ሪክ ማቻር (ዶ/ር) መካከል ያለውንና ጉዳት እያስከተለ ያለውን ልዩነት ለመፍታት፣ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዓርብ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በጁባ ውይይት አደረጉ፡፡  

በሙስና የተከሰሱት የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ

የመንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎች መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ተቀጠሩ በሙስናና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን ወ/ሮ ፀዳለ ማሞን ጨምሮ፣ 13 ተከሳሾች ዓርብ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

ደኢሕዴን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የመፍታት ችግሮች እንደነበሩበት ገለጸ

የኢሕአዴግ አባል ድርጅት የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን)፣ ባለፈው ዓመት በክልሉ ውስጥ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን  በወቅቱ የመፍታት ችግሮች እንደነበሩበት አስታወቀ፡፡

ህፃናትን በበጉዲፈቻ ወደ ውጭ አገር መላክ የሚፈቅደው አንቀጽ ከኢትዮጵያ ቤተሰብ ሕግ እንዲሠረዝ ተወሰነ

የውጭ አገር ጉዲፈቻ የተፈጥሮ ቤተሰብ ፍቅርና እንክብካቤን ሙሉ በሙሉ የማይተካና ከዚህ ቀደም በጉዲፈቻ ወደ ውጭ አገራት የሄዱ ህፃናት ላይ የማንነት ቀውስ በማስከተሉ፣ ይህን አሠራር የሚፈቅደው የሕግ ድንጋጌ ከቤተሰብ ሕጉ እንዲሠረዝ መንግሥት ወሰነ።