Skip to main content
x

ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር በህዳሴ ግድቡ ተፅእኖዎች ላይ እየመከረች ነው

የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የውኃ ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ውኃ አሞላልና ግድቡ በታችኛው የአባይ ተፋሰስ አገሮች ላይ ሊኖሩ በሚችሉ ተፅእኖዎች ላይ በኢሊሊ ሆቴል ዛሬ እየተወያዩ ነው፡፡

መቋጫ ያጣው የሦስቱ አገሮች ድርድርና የህዳሴ ግድብ

ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ከጣለች ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የግንባታ ሒደቱም 60 በመቶ እንደደረሰ ተነግሯል፡፡ የህዳሴ ግድቡን የመሠረት ድንጋይ በተጣለ ማግሥት ግብፅ ግድቡ ዕውን እንዳይሆን ሙሉ አቅሟን ተጠቅማ ስትንቀሳቀስ ነበር፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ስለምስክሮች ጥበቃ የወጣው አዋጅ ከሕገ መንግሥቱ ጋር አይጋጭም ተባለ በሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ላይ ወንጀል በመፈጸም፣ የሐሰት ወሬ በማውራትና በወቅቱ ተደንግጎ የነበረን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመተላለፍ ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ጥቅምት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት ሰጡ፡፡

የኦሮሚያና የሶማሌ ግጭት በወጪና በገቢ ንግድ መተላለፊያ መስመር ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተገለጸ

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት፣ በወጪና በገቢ ንግድ መተላለፊያ መስመር ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠሩን፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

አቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡትን መልቀቂያ መንግሥት እየተመለከተው ነው

ላለፉት 26 ዓመታት በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በኃላፊነት የቆዩት ነባሩ የኢሕአዴግ አመራር አቶ በረከት ስምኦን፣ ሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ከኃላፊነተቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ መንግሥት እየተመለከተው መሆኑ ተገለጸ፡፡

የካርታ ሥራና የታብሌት ኮምፒዩተር ግዥ መዘግየት የሕዝብና ቤት ቆጠራውን እንዳራዘመ ተገለጸ

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የካቲት 4 ቀን 2010 ዓ.ም ለሚደረገው አራተኛው የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ በቅርቡ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ሥፍራዎች በተፈጠረው ግጭት በሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀል በቆጠራው ላይ ተፅዕኖ እንደማይፈጥር ገለጸ፡፡ የካርታ ሥራ፣ የታብሌት ኮምፒዩተርና የፓወር ባንክ ግዥ መጓተት ለመዘግየቱ በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡

የሶማሌላንድ ጉዳይ ፈጻሚ ጽሕፈት ቤትን በማቃጠል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን የሶማሌላንድ መንግሥት ጉዳይ ፈጻሚ ጽሕፈት ቤትን በማቃጠል ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡ ተጠርጣሪው ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለውና በቅርቡ ከሶማሌላንድ ዋና ከተማ ሐርጌሳ ተፈናቅሎ እንደመጣ ለፖሊስ ማስረዳቱን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የፖሊስ ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል የተባሉት ሁለት የጉምሩክ ሠራተኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በ2004 እና በ2005 በጀት ዓመት መከፈል የነበረበትን ግብር ሳይከፍሉ በመቅረታቸው አራት ሚሊዮን ብር ይከፍላሉ ከተባሉ ግብር ከፋይ 400 ሺሕ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል የተባሉ፣ ሁለት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

በባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኃላፊዎች ላይ የክስ መመሥረቻ የመጨረሻ ጊዜ ተሰጠ

ሁለት ተጠርጣሪዎች ከፖሊስ ጣቢያ ተለቀ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ላለፉት ሁለት ወራት በምርመራ ላይ በነበሩት የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ኃላፊዎች ላይ፣ ዓቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሠረት የመጨረሻ 15 ቀናት ተሰጠው፡፡ የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን ጎን ለጎን ቀረኝ የሚለውን ምርመራ እንዲያካሂድም ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡