Skip to main content
x

አቅጣጫ ያልጠቆመው የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባ

እሑድ ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ የሚገኘው የመብራት ኃይል አዳራሽ ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ ሦስት ወራት ያህል ከፈጀ ውትወታና ምልልስ በኋላ፣ በመንግሥት ዕውቅና የተሰጠው ሕዝባዊ ስብሰባ ለመታደም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

በአንድ ቀን ይጠናቀቃል የተባለው የኦሕዴድ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ ለአራት ቀናት ተራዝሟል

በአዳማ ከተማ ገልማ አባገዳ እየተካሄደ ያለው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሰባተኛ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ በአንድ ቀን ይጠናቀቃል ተብሎ ዕቅድ ቢያዝለትም፣ አራት ቀናት ጨምሮ እስከ ሐሙስ ጥቅምት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚቆይ ታወቀ፡፡

በኦሮሚያ ልዩ የፖሊስ አደረጃጀት አለመኖሩን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ

የአማራና የሶማሌ ክልሎች መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ‹ልዩ ኃይል› የሚባል የፖሊስ አደረጃጀት እንደሌለው፣ ይህ ስም ለአድማ ብተና ኃይል እንደሚሰጥ የክልሉ ፖሊስ ገለጸ፡፡ የአማራና የሶማሌ ክልሎች መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ስምንት ሰዎች እንደ ሞቱ ክልሉ አስታወቀ

ሌሎች ምንጮች ቁጥሩን ከፍ አድርገዋል ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን ሃሮ ዴዴሳ ቀበሌ በተነሳው ግጭት ስምንት ሰዎች መሞታቸውን ክልሉ አስታወቀ፡፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መንግሥቱ ቴሶ የሟቾች ቁጥር ስምንት ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ስምንት ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በነቀምቴ ከተማ ሦስት ሰዎች ተገደሉ

ሁለት ባጃጆች ሙሉ በሙሉ ሲቃጠሉ በአንድ ሆቴል ላይ ጉዳት ደርሷል በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ወርቁ ጫላ ማክሰኞ ጥቅምት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ እሑድ ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በከተማዋ የኢሬቻ በዓል ሲከበር ቦምብ ይዘው የመጡ ወጣቶች አሉ በሚል ሰበብ በተነሳው ግጭት ሁለት ሰዎች ሞተዋል፡፡ ሟቾችም በእውቀቱ ውበት ሙሉጌታ፣ ደገባስ ፈቃደ ካባና ኤርሚያስ ባዩ ምትኬ እንደሚባሉ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት በየዓመቱ ለሠራተኞች የደመወዝ እርከን ማሻሻያ ለማድረግ አቅም የለኝም አለ

ሠራተኞች የጳጉሜን ወር ክፍያ እንዲያገኙ የቀረበው ጥያቄም ተገቢነት የለውም ብሏል የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች በየዓመቱ የደመወዝ እርከን እንዲያገኙ በሕግ እንዲወሰን የቀረበውን ጥያቄ ተግባራዊ ለማድረግ፣ የአገሪቱም ሆነ የመንግሥት አቅም እንደማይፈቅድ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አቶ በቀለ ገርባ በሥር ፍርድ ቤት ዋስትና የተከለከሉት ያለበቂ ምክንያት እንደሆነ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ፣ በሥር ፍርድ ቤት የዋስትና መብት የተነፈጋቸው ያለበቂ ምክንያትና የተለወጠላቸው የሕግ ድንጋጌ ግምት ውስጥ ሳይገባ መሆኑን በመጥቀስ፣ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ወሰነ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱን ሰንገው ስለያዟት ግጭቶች ማብራሪያ የሰጡበት የፓርላማ ውሎ

መስከረም 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑን በአገሪቱ ፕሬዚዳንት የመክፈቻ ንግግር የጀመረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባውን ለማካሄድ፣ ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰይሟል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ 30 ሰዎች ሞተዋል

240 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል በኦሮሚያ ክልል በቡኖ በደሌ ዞንና በአምቦ ከተማ በአንድ ሳምንት ውስጥ 30 ሰዎች ሲሞቱ፣ 37 ያህል ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቡኖ በደሌ ዞን በገቺ፣ በደሌ፣ ጮራና ዴጋ ወረዳዎች ጥቅምት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ግጭት መቀስቀሱ የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህ ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 20 መድረሱ ተገልጿል፡፡

ሐበሻ ሲሚንቶ በገጠመው የፀጥታ ችግር ማምረት አቆመ

የዳንጎቴ ሲሚንቶ አምስት ተሽከርካሪዎች ተቃጠሉ በኢትዮጵያ ባለአክሲዮኖች ተገንብቶ በሚያዝያ 2009 ዓ.ም. ምርት የጀመረው ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር በገጠመው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከማክሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ማምረት ማቋረጡ ተሰማ፡፡