Skip to main content
x

ሼክ አል አሙዲ ታስረው እየተመረመሩ ነው

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ በተጀመረው ፀረ ሙስና ዘመቻ ታስረው እየተመረመሩ ነው፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያን ፀረ ሙስና ዘመቻ የሚመሩት የአገሪቱ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ቅዳሜ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ በታዋቂው ሪትዝ ካርልተን ሆቴል በቁጥጥር ሥር ካዋሏቸው 11 ልዑላንና 38 ታዋቂ ባለሀብቶች መካከል አንዱ የሆኑት ሼክ አል አሙዲ፣ በሙስና ተጠርጥረው እየተመረመሩ ይገኛሉ፡፡

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማብራሪያ ተሰጠ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ፣ ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በተዘጋጀ መድረክ ማብራሪያ ሰጡ፡፡

በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩና የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ

‹‹የምስክር ትንሽ ትልቅ የለውም›› አቶ በቀለ ገርባ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው የሽብር ተግባር ወንጀልና ከባድ የማነሳሳት ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ በቀለ ገርባ፣ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር ሦስት ሠራተኞች ተከሰሱ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 10 ውስጥ የሚገኝ በ413 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ባለ አምስት ፎቅ ሕንፃ ላይ የተሰጠ ውክልና የተሻረና በክፍለ ከተማው ተመዝገቦ እያለ፣ የተሰጠው ሕጋዊ ውክልና እንዳልተነሳ አስመስለው ለባንክ ማረጋገጫ በመስጠት ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ሦስት የክፍለ ከተማው የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ተከሰሱ፡፡

ሼክ አል አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ በቁም እስር ላይ ናቸው

​​​​​​​የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀ መንበር ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ በተጀመረው ፀረ ሙስና ዘመቻ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል አንዱ መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡ ሼኩ በአሁኑ ጊዜ በሳዑዲ ዓረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኘው ታዋቂው ሪትዝ ካርልተን ሆቴል በቁም እስር ላይ ናቸው፡፡

የአቶ በቀለ ገርባ ዋስትና መታገድ እያነጋገረ ነው

ከአንድ ዓመት በፊት በሽብር ተግባር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ፣ የተከሰሱበት የሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ ተቀይሮ ዋስትና ቢፈቀድላቸውም ሳይለቀቁ በይግባኝ መታገዱ እያነጋገረ ነው፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አካባቢያዊ ፋይዳ

በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል ያለው ግንኙነት ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታን የመሠረት ድንጋይ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም. ከጣለች በኋላ ይበልጥ ተወሳስቦ ነበር፡፡ ግድቡ በሁለቱ አገሮች ላይ መሠረታዊ ጉዳት ያስከትላል? አያስከትልም? የሚለው ጉዳይ አዲስ የውዝግብ አጀንዳ ሆኖ ነበር፡፡ መጀመርያ ላይ ሁለቱም ግድቡን ተቃውመው እንዲቆም ጠይቀው ነበር፡፡

የኦሕዴድ ኮንፈረንስ የአሥር ዓመት ድርጅታዊ ስትራቴጂ በማውጣት ተጠናቀቀ

በአዳማ ከተማ ገልማ አባ ገዳ አዳራሽ ሲካሄድ የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ኮንፈረንስ፣ የአሥር ዓመት ድርጅታዊ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ተጠናቀቀ፡፡ የኦሮሚያ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ለሪፖርተር እንደተናገሩት የክልሉን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ የአሥር ዓመት የድርጅቱ ስትራቴጂ ይፋ ሆኗል፡፡

በፌዴራል መንግሥት የተረቀቀው የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ አዋጅ እንዳይፀድቅ የኦሮሚያ ክልል ጠየቀ

በፌዴራል መንግሥት ተረቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበውና በአገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ እንዲደረግ ሆኖ የተዘጋጀው የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ አዋጅ እንዳይፀድቅ፣ የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ጠቅላይ ሚንስትሩንና ፓርላማውን በደብዳቤ ጠየቀ።