Skip to main content
x

ተቃዋሚዎች ገሸሽ የሚያደርጉት ኢሕአዴግ ብቻውን የሚያሸንፍበት አካባቢያዊ ምርጫ

አገሪቱን ባለፉት ሦስት ዓመታት ከገጠማት የፖለቲካ ቀውስና አለመረጋጋት ለማውጣት መንግሥት የተለያዩ ዕርምጃዎች እየወሰደ ቢሆንም፣ ችግሮቹ መልካቸውን እየቀያየሩ የቀጠሉ ይመስላል፡፡ የ‘ጥልቅ ተሃድሶ’ የፓርቲና የመንግሥት ግምገማ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ አስተዳደራዊ ዕርምጃዎችና የፀረ ሙስና ዘመቻዎች አገሪቱን ወደ ነበረችበት መረጋጋት መልሰዋታል ለማለት አዳጋች ነው፡፡

ወደ ከፍታው ዘመን ለመድረስ የቱ ይበጀናል?

‹‹ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል” ወይስ “እናውቃለን ብንናገር እናልቃለን››? ‹‹እኔ በአንድ ወቅት በፈጸምኩት ወንጀል ምክንያት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶብኝ ቅጣቴን በመፈጸም ላይ ነኝ፡፡ የዕድሜ ልክ እስራት ፍርደኛ መሆኔ ግን በማረሚያ ቤቱ ውስጥ የማያቸውን የአስተዳደር ችግሮችም ሆነ በታራሚዎች ዘንድ የማየውን ግድፈት ከመናገር አያስቀረኝም፡፡

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነው

በቅርቡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ደም አፋሳሽ ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት፣ የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነው፡፡ ኮንፈረንሱን ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡

የመንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎች ከሁለት ደረጃ አንድ ሥራ ተቋራጮች ጋር ክስ ተመሠረተባቸው

ለሁለቱም ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ክፍያ መፈጸሙ ተገልጿል ሳትኮንና ሀዚ አይአይ ሥራ ተቋራጮች በክሱ ተካተዋል ከሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ሲካሄድባቸው በከረሙት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሰባት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገምሹ በየነ (በሌሉበት) እና በዲኤምሲ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ማሞ (በሌሉበት) ላይ ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡

ፍርድ ቤት ለዓቃቢያነ ሕግ የመጨረሻ የተግሳጽ ቅጣት ሰጠ

በገንዘብ ሚኒስቴርና በስኳር ኮርፖሬሽን ተጠርጣሪዎች ላይ የመጨረሻ ቀጠሮ ተሰጠ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት፣ ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዓቃቢያነ ሕግ ላይ የመጨረሻ የተግሳጽ ቅጣት ሰጠ፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኦሮሚያና በሶማሌ አዋሳኝ ሥፍራዎች የተከሰተው ግጭት አሳስቦናል አሉ

የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰሞኑን በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ሥፍራዎች የተከሰተው ግጭት በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳስባቸው፣ መንግሥትም በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠውና በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ አመራሮችና ግለሰቦች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥያቄ አቀረቡ፡፡

መንግሥት የቋንቋ ፌዴራሊዝም ሥርዓቱን እንዲፈትሽ ኢዴፓ ጠየቀ

መንግሥት በፌዴራል ሥርዓቱ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ፖለቲካዊ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ፣ በጊዜያዊ መፍትሔ ላይ ያተኮረ ዕርምጃ መውሰድ ላይ በማተኮሩ ውጥረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የአገሪቱን ህልውና የሚፈታተን ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን የገለጸው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የቋንቋ ፌዴራሊዝም ሥርዓቱን መንግሥት እንዲፈትሽ ጠየቀ፡፡

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ሰባት ኃላፊዎችና አንድ ባለሀብት ተከሰሱ

የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያላግባብ በመገልገልና ከሥልጣቸው በላይ በመጠቀም ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በመንግሥትና ሕዝብ ሀብት ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ፣ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በተለያዩ የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ሰባት ኃላፊዎችና አንድ ባለሀብት ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

ኢትዮጵያ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ያቀረበችው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የውሳኔ ሐሳብ ያለተቃውሞ ፀደቀ

ግብፅ ድጋፏን ሰጥታለች በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 72ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ጉባዔ ላይ፣ ኢትዮጵያ ራሷ አዘጋጅታ ያቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ ያለምንም ተቃውሞ መፅደቁ ተነገረ፡፡ አጀንዳው ሰላም ማስከበርን የተመለከተ ነው፡፡

መሻሻሎችን አሳይቷል የተባለው የኦሮሚያና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች ጉዳይ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መካከል ተቀስቅሶ የነበረውን ግጭት ለማብረድ፣ ባለፈው ሳምንት የፌዴራሉ መንግሥት የፀጥታ አካላት ወደ ሥፍራው መሄዳቸው ይታወቃል፡፡