Skip to main content
x

የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ችግሩ መፍትሔ ሲያገኝ ወደ ቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው እንደሚመለሱ ተገለጸ

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የሁለቱ ክልሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየክልሎቻቸው እንዲመደቡ የተደረጉት በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ እንጂ በክልሎች ጣልቃ ገብነት አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ ምሁራን በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ተወያዩ

የኢትዮጵያና የኤርትራን ሕዝብ የወደፊት ግንኙነት በተመለከተ ከሁለቱ አገሮች የተወከሉ ምሁራን በአዲስ አበባ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ‹‹የሰላም መዝሙር ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ሕዝቦች›› በሚል መሪ ቃል ሐሙስ ኀዳር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በሐርመኒ ሆቴል በተካሄደው ውይይት ላይ፣ ኤርትራን በመወከል ከአውሮፓ የመጡና በአዲስ አበባ የሚኖሩ ምሁራን ተገኝተዋል፡፡ በውይይቱም የሁለቱን አገሮች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የገቱ ጉዳዮች ተነስተው ተመክሮባቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ መጥሪያ ሊደርሳቸው ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ፡፡

አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ አዲሱ ቡላ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሩዋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳና ምክትላቸው አቶ አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሲሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ቀደም ብሎ ምስክሮቹ ያልቀረቡበት ምክንያት ሬጅስትራር ማዘዣ ወጪ ሳያደርግ በመቅረቱ እንደሆነ አስረድቶ አሁን ግን ማዘዣ ወጪ እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

መከላከያ ምስክሮቹም ታህሳስ 17፣ 18 እና 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀርበው እንዲሰሙ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

‹‹የኦሮሚያን ተማሪዎች ከጅግጅጋ የሶማሌን ክልል ተማሪዎች ከኦሮሚያ ውጪ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች መመደብን አላምንበትም››

አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ናቸው፡፡ ክልሉን ላለፉት ስድስት ዓመታት መርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲስተካከል እንግሊዝ ጥያቄ አቀረበች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ እየተፈጠሩ ያሉ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮች እንዲስተካከሉ እንግሊዝ ጠየቀች፡፡   ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ እየተከሰተ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግር እንዳለ፣ ኢትዮጵያም ይህን ችግር እንድታስተካክል እንግሊዝ ምክረ ሐሳብ ማቅረቧ ታውቋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር በፀጥታ ችግሮች ሳቢያ መቀነሱ አሳስቦኛል አለ

በዩኒቨርሲቲዎች የተቋረጠው የታሪክ ትምህርት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ ተወሰነ ከመስከረም ወር ጀምሮ በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት የሚጠበቅባቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር መቀነሱ እንዳሳሰበው፣ ትምህርት ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ።

ኢትዮጵያና ኳታር ዲፕሎማቶቻቸው ያለ ቪዛ እንዲንቀሳቀሱ ተስማሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከሰኞ ኅዳር 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኳታር በመሄድ፣ በማግሥቱ ከኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሀማድ አልታኒ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለቱ አገሮች ዲፕሎማቶች ያለ ቪዛ እንዲንቀሳቀሱ ተስማሙ፡፡

አምባሳደር ዶናልድ ያማማቶ በኢትዮጵያ የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች ኢኮኖሚያዊ መነሻ አላቸው አሉ

ኢትዮጵያና ኤርትራን ለመሸምገል አሜሪካ ቁርጠኛ ናት ብለዋል የቀድሞው የኢትዮጵያና የኤርትራ አምባሳደር፣ የአሁኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ምክትል ኃላፊ ዶናልድ ያማማቶ፣ በኢትዮጵያ እየተከሰቱ የሚገኙ የፀጥታ ችግሮች ኢኮኖሚያዊ መነሻዎች አሉዋቸው አሉ፡፡ አገሪቱ ከሶማሊያ የሚቃጣባት የሽብር አደጋም አሳሳቢ ሆኖ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

የቀድሞ የአንበሳ አውቶቡስ ድርጅት ኃላፊዎችና ሠራተኞች በ55.7 ሚሊዮን ብር የሙስና ወንጀል ተከሰሱ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ኃላፊዎችና ሠራተኞች የነበሩ 11 ሰዎች፣ በሕዝብና መንግሥት ላይ ከ55.7 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የሙስና ክስ ተመሠረተባቸው፡፡