Skip to main content
x

በመጤ አረም የተወረረው አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ

የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ በመጤ አረም መወረሩን የፓርኩ ኃላፊ አቶ ሽፈራው መንግሥቴ ይናገራሉ፡፡ ይህም ከሰው ሠራሽ ችግሮች ጋር ተዳምሮ የፓርኩን ህልውና እየተፈታተነ ነው፡፡ አቶ ሽፈራው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ፕሮሶፊሶ ፓርቴንየምና ሪቨር ቫይን በመባል በሚጠሩት መጤ አረሞች ፓርኩ በመጥለቅለቅ ላይ ሲሆን፣ በነፋስና በእንስሳት ዓይነ ምድር አማካይነት በፍጥነት እየተዛመተም ነው፡፡

በመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት መስክ ለውጦችን ያመላከተው የስታትስቲክስ ኤጀንሲ ጥናት በርካታ ጉድለቶች እንዳሉ ጠቆመ

በለጋሾችና በኢትዮጵያ መንግሥት በሚመደብ በጀት ሲተገበሩ በቆዩት የመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ በየጊዜው ለውጦች ቢመዘገቡም፣ በርካታ ጉድለቶች እንደሚታዩ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ጥናት አመላከተ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ረገድ አፋርና ሶማሌ ክልሎችና የድሬዳዋ አስተዳደር ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ለግንባታዎች የወጣው የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሰርኩላር እንዲነሳ ተደረገ

በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የተቋቋመው ዴሊቨሪ ዩኒት ማናቸውም ግንባታዎች ከመካሄዳቸው በፊት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እንዲያካሂዱ አስገዳጅ ሆኖ መደንገጉ ለመልካም አስተዳደር ዕጦት ምክንያት ሆኗል የሚል አቋም በመያዙ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲል ፕሮጀክቶች ከመካሄዳቸው በፊት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የማካሄድ ጉዳይ አስገዳጅ ስለመሆኑ ያስተላለፈውን ሰርኩላር አነሳ፡፡

የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት አተትን መከላከል እንዳልቻለ ተገለጸ

የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት አተትን መከላከል እንዳልቻለ የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ ይህ የተገለጸው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ጉባዔውን ከጥቅምት 28 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታት የአተት በሽታ በአገሪቱ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰም በጉባዔው ተጠቁሟል፡፡

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና በንጉሥ ኦላቭ ሃኮን የተጠነሰሰው ወዳጅነት

ኢትዮጵያን ከሌሎች የአፍሪካ ቅኝ ግዛት አገሮች ጎራ የማድረግ ትልቅ ህልም የነበረው የጣሊያን መንግሥት በዓደዋ ጦርነት ድል ቢነሳም አርፎ መቀመጥ አልሆነለትም፡፡ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ግዛቱን ለማስፋፋት መልሶ ዓይኑን ኢትዮጵያ ላይ ጣለ፡፡ በ1927 ዓ.ም. ወልወል ላይ በሁለቱ አገሮች ወታደሮች መካከል በተነሳ ግጭት ከሁለቱም ወገን የሰው ሕይወት ጠፋ፡፡

ኢትዮጵያና ኖርዌይ ወረርሽኝን ቀድሞ በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

ኢትዮጵያ፣ ከዓርባ ዓመታት በላይ በጤና፣ በትምህርት፣ በልምድ ልውውጥና በተለያዩ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ስትሠራና ስትረዳ ከቆየችው ኖርዌይ ጋር፣ በዓለም ሊከሰቱና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሊያጠፉ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ወረርሽኞችን ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ሥራ ለመሥራት ከስምምነት ደረሰች፡፡

በአዲስ አበባ የተንሰራፋውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኅብረተሰቡ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች ለመፍታት በ13 መሥሪያ ቤቶች ላይ ባካሄደው ጥናት፣ 211 ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ዝርዝር የመፍትሔ ሐሳቦችን አቀረበ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ3.4 ቢሊዮን ብር የ850 አውቶብሶች ግዥ ፈጸመ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው የተንሰራፋውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት በ3.4 ቢሊዮን ብር የ850 አውቶብሶች ግዥ ፈጸመ፡፡ ከነዚህ አውቶብሶች መካከል 150 የሚሆኑት አገር ውስጥ ገብተው በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ በመገጣጠም ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከእነዚህ አውቶብሶች ውስጥ 100 የሚሆኑት በሸገር ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አማካይነት ለተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡

የመሠረተ ልማት ተቋማት በቅንጅት ለመሥራት ተስማሙ

ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ዓመት 700 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ዝርጋታ ያካሄዳል በፌዴራል መንግሥትና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ የመሠረተ ልማት ተቋማት፣ ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባ የሚያከናውኗቸውን ግዙፍ ፕሮጀክቶች በመናበብ ለመገንባት ረቡዕ ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ኢትዮጵያ ከዳያስፖራ ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ አገኘች

በተለያዩ ውጭ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዓምና (2009 ዓ.ም.) 4.6 ቢሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ከፍተኛ የውጭ የምንዛሪ ምንጭ ሆነው እያገለገሉ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራና ቢዝነስ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አስታወቁ፡፡