Skip to main content
x

ኢኮኖሚስቱ ኬንስ ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ምን ይል ነበር?

አዳም ስሚዝ በ18ኛው ክፍለ ዘመን በገበያ ውስጥ በምርት ፍላጎትና አቅርቦት መስተጋብር በሚፈጠር የምርት ዋጋ ከፍና ዝቅ ማለት ትርፋማነት ድርጅቶች ሠራተኛ ለመቅጠርና ላለመቅጠር በሚወስዱት ውሳኔ ሥራ አጥነት ይጨምራል፣ ይቀንሳል የሚል የግል ኢኮኖሚ ትንታኔ (Microeconomic Analysis) ሰጥቶ የሊበራል ገበያ ኢኮኖሚን በመተንተን የኢኮኖሚክስ አባት ሆነ፡፡

አገር የሚያድነው ዴሞክራሲያዊነት ብቻ ነው!

የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ከሚያጓጓ ተስፋ ወደ አስከፊ ሁኔታ መንሸራተት የታየበት ነው፡፡ በእርግጥም እየታያ ያለውን የፖለቲካ ቀውስ፣ አለመተማመንና ሕዝባዊ ሥጋት ሕዝቡ፣ መንግሥት፣ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና የሲቪክ ማኅበራት ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ ተደማምጠው ካልፈቱት መካረሩና መቋሰሉ ይዞን ወደ ማጥ ላለመግባቱ ዋስትና የለም፡፡

በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ መግባባት ለምን ያቅተናል?

በዚህ አገር ውስጥ የምንኖር ሕዝቦች ታሪክ የውድቀትም ይሁን የድል፣ የዕድገትም ይሁን የክሽፈት በየዘመኑ በነበሩ አባቶች ጥልቅ አገራዊ ስሜት አብሮነት የተገነባ መሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ በገዥዎች መካከል በነበረ የግዛት ማስፋፋትም ይባል፣ እርስትና ግብርን የማብዛት ህልም ጦርነቶች እየተካሄዱ የሰውም የንብረትም ጥፋት (በየትኛውም ዓለም የነበረ የኃያልነት ፍልሚያ የወለደው ቢሆንም) ተፈጽሟል፡፡ በዚህ ሒደትም ሕዝቡ እንደ ሕዝብ ተሳስሮና ተባብሮ ከመኖር ያገደው አልነበረም፡፡

ሶማሊያን የሚያውቅ በሰላም ጉዳይ አይደራደርም!

ለሽብርና ለአክራሪነት መነሻ እየሆነ የመጣ ፅንፈኛ አስተምህሮ በተለያዩ የዓለም አገሮች ታይቶ ከመቻቻልና መከባባር ባፈነገጠ መንገድ ለዕልቂትና ውድመት መንስዔ ሆኗል፡፡ በተለይ በየቀጣናው በሚፈጠሩ ፅንፈኛ ቡድኖች (አልቃይዳ፣ አይኤስ፣ ቦኮ ሐራም፣ አልሻባብ፣  . . . ) ዓይነቶችና የጥፋት ኃይሎች ብዙ ሕዝቦች ለዕልቂትና ለውድመት ተጋልጠው ቆይተዋል፡፡ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ ሶማሊያንም የገጠማት ይኼው ነበር፡፡

ገደብ ያልተበጀለት የቤት ኪራይ ጭማሪና የተከራዮች እሮሮ

 ‹‹አዲስ አበባ በትልቅ የእግር ኳስ ሜዳ ትመሰላለች›› ያለው ማን ነበር? ድሆች በዙሪያ ተኮልኩለው ሲመለከቱ ሀብታሞች መሀል ላይ ይጫወታሉ፡፡   ለማንኛውም ይህ ጽሑፍ ‹መሀል ከተማ የነበረን ቤት ለሀብታም ተሰጥቶ ለእኛ ከከተማ ጫፍ ተሰጠን. . . ባማረው ሰፊ ግቢ ምትክ በኮንዶሚኒየም ብቻ ሸነገሉን. . .› ስለሚሉ ባለካርታ ሰዎች አይደለም፡፡

የኢሕአዴግ ከራስ ጋር ኩርፊያና ፖለቲካዊ አንድምታው

ኤድዋርድ ጊቢን የመካከለኛዋን ዘመን ኢትዮጵያ ሲገልጽ ‹‹ዓለምን ረስታ፣ በዓለምም ተረስታ፣ በጠላት ተከባ በሮቻን ዘግታ ለሺሕ ዘመናት ያንቀላፋች አገር፤›› ይላታል፡፡ ይህ ዓይነቱ አገላለጽ ከዛሬው ዘመን የፖለቲካ ጉዞችን ጋር ኩታ ገጠም ነው፡፡ ኢሕአዴግ በውስጥና በውጭ ጠላቶቹን ተከቦ፣ ስለ እሱ ማወቅ የሚፈልጉ ዜጎቹንም ረስቶ በሮቹን ዘግቶ አንቀላፍቷል፡፡

ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ከፕሮፓጋንዳ ተላቆ ለአገር ግንባታ ይዋል

አገራችን ኢትዮጵያ ቋሚና ብዙ ታሪክ ያለው ሰንደቅ ዓላማ ካላቸው አገሮች ግንባር ቀደም ናት፡፡ ይሁንና ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላ አወዛጋቢ የሆኑ ቃላት በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊና በሕገ መንግሥቱ ረቂቅ ክርክር ላይ በተለያዩ ግለሰቦች ስለተነሱ፣ ኅብረተሰቡ ስለሰንደቅ ዓላማ የነበረውን አመለካከትና እምነት እንዲሸረሸር፣ ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ያለው እምነት በጥርጣሬ ዓይን እንዲታይ የበኩሉን ድርሻ ነበረው፡፡

ከፍታና መንጠራራት

ስለመንጠራራት ሳስብ ቃሉ በራሱ ቅኔ ይመስለኛል፡፡ አንድም መንጠራራት ማለት ከእንቅልፋችን ስንነሳ አሊያም በሥራ ሰንደክም እጃችንን ወደ ጎንና ወደ ላይ በመወጠርና በመለጠጥ የምናሳየው እንቅስቃሴ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ መንጠራራት ማለት ወደ ላይ የማይደርሱበትን ቦታ፣ የሆነ ከፍ ያለን ሥፍራ መመኘት ወይም ያላቅሚቲ መፍጨርጨርን የሚገልጽ ይመስለኛል፡፡ በሁለቱም ትርጓሜዎች ብንሄድ አንድ የሚያሳየን ነገር ይኖራል፡፡