Skip to main content
x

‹‹የምርጫ ሥርዓታችን ትልቁ ፈተና ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ የማካሄድ እንጂ የመወከል ጉዳይ ነው ብዬ አላምንም››

አቶ ሙሼ ሰሙ፣ የቀድሞ የኢዴፓ ፕሬዚዳንትና አንጋፋ ፖለቲከኛ አቶ ሙሼ ሰሙ የቀድሞው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከማንኛውም የፓርቲ ፖለቲካ ራሳቸውን ያገለሉ ቢሆንም፣ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ስለአገሪቱ ፖለቲካና ሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች በግላቸው ሐሳቦችን ይሰነዝራሉ፡፡ ከፓርቲ ፖለቲካ ሙሉ በሙሉ የተገለሉት አቶ ሙሼ በአንድ የግል ባንክ በኃላፊነት በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

‹‹አዲስ አመራር በመጣ ቁጥር የቀድሞውን እያፈረሱ ከመሄድ ይልቅ የተጀመረውን ማስቀጠል ይመረጣል››

አቶ መላኩ እዘዘው (ኢንጂነር)፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አዲሱ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከ70 ዓመታት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል፡፡ አንጋፋ ከሆኑ መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ተርታ የሚሠለፈው ይህ ንግድ ምክር ቤት፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ አመራር ለመምጣት በሚሹ ወገኖች ይደረጋል በተባለ ሽኩቻ ስሙ ሲነሳ ቆይቷል፡፡ በተለይ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫዎች በሚካሄዱበት ወቅት ተደጋጋሚ ውዝግቦችና ቅሬታዎች ሲስተዋሉ እንደነበር ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ በተደረገው ምርጫ ከበፊቶቹ በተሻለ ያለ ውዝግብ ተፈጽሟል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ለደን ያደላ ኢኮኖሚ ብትመሠርት ኖሮ ይህን ያህል የምግብ ዋስትና ችግርም ሆነ ድህነት ይኖራል ብዬ አልገምትም››

ሙሉጌታ ልመንህ (ዶ/ር)፣ በፋርም አፍሪካ የምሥራቅ አፍሪካ የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኃላፊ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በደን ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪቸውን ያገኙት ሙሉጌታ ልመንህ (ዶ/ር)፣ ከኔዘርላንድስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሲያገኙ፣ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ በስዊድን ተከታትለው በመምጣት ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ የደን ሳይንስ መስክ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ ጊዜ ውስጥ 18 ዓመታትን ያሳለፉት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በደን ሳይንስ መስክ በማስተማር እንደሆነ ገልጸው፣ የወንዶ ገነት የደን ምርምር ማዕከልን ተቀላልቀው ከማስተማር ባሻገር 90 የሚደርሱ በርካታ ምርምሮችን ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር ሲያከናውኑና የምርምር ውጤቶቻቸውንም ሲያሳትሙ ቆይተዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ እስካሁን የሚመጥናትን ፖለቲካ አላገኘችም››

አቶ ገብሩ አሥራት፣ አንጋፋ ፖለቲከኛ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ አካጂጃለሁ ባለና ከሁለት ዓመት በፊት ለተነሳ ሕዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ጀምሬአለሁ ባለ ማግሥት አዳዲስ የፖለቲካ ክስተቶች መታየት ጀምረዋል፡፡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል በተነሳ ግጭት በአሰቃቂ መንገድ የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፡፡ በርካቶች ተፈናቅለዋል፡፡

‹‹በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ለኢትዮጵያ አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር የማቅረብ ፍላጎት አለን››

አቶ አድማሱ ይልማ፣ የኮሜሳ የንግድና የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት   አቶ አድማሱ ይልማ ታደሰ የኢኮኖሚ ባለሙያ ብቻ ሳይሆኑ፣ በአፍሪካ ከፍተኛ ተቀባይነት ካገኙ የባንክ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች መካከል የሚመደቡ ናቸው፡፡ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ከዚህ ቀደም የደቡብና ምሥራቃዊ አፍሪካ አገሮች የጋራ ገበያ ባንክ (ፒቲኤ ባንክ) እየተባለ የሚጠራውን ተቋም፣ ወደ ኮሜሳ ንግድና ልማት ባንክ እንዲለወጥ አድርገዋል፡፡

‹‹ለአገሪቱ ሶሽዮ ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩላችንን አስተዋጽኦ እያደረግን ነው››

አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ከአሜሪካው ትራንስ ወርልድ ኤርላይን ጋር በገባው ውል እ.ኤ.አ. 1945 የተመሠረተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚ አየር መንገድ ነው፡፡

‹‹መፍታት የሚገባንን የወሰንና የመሳሰሉት ችግሮች ባለመፍታታችን እንጂ የሰሜን ጎንደር ሰው መሣሪያ ስለታጠቀ አይደለም አመፅ ተቀስቅሶ የነበረው››

አቶ አየልኝ ሙሉዓለም፣ የቀድሞው ሰሜን የአሁኑ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ በ2008 ዓ.ም. ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲነሳባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል አንዱ ሰሜን ጎንደር ዞን ነው፡፡ በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው ሁከት ከስድስት መቶ በላይ ዜጎች ሕይወት መጥፋቱና ንብረት መውደሙ ይታወሳል፡፡

‹‹በአገሪቱ አካባቢያዊ ዴሞክራሲ ለማስፈን የአካባቢያዊ አስተዳደሮችን ሥልጣንና ተግባር በግልጽ ማስቀመጥ የግድ ይላል››

ዶ/ር ዘመላክ ዓይነተው፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ጥናት ማዕከል መምህር ዶ/ር ዘመላክ ዓይተነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ጥናት ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ሲሆኑ፣ በዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርሲቲ ዱላህ ኦማር ኢንስቲትዩት ኤክስትራኦርዲናሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ ዶ/ር ዘመላክ በአካባቢያዊ አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረጉ የሕገ መንግሥት ኤክስፐርት ናቸው::

‹‹ለዋናው ችግራችን መፍትሔ አግኝተናል ወይ የሚለው ያሳስበኛል››

አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ፣ የኅብረት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ታዋቂው የኢንሹራንስ ባለሙያ አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ የ79 ዓመት አዛውንት ናቸው፡፡ ከግማሽ ምዕት ዓመት በላይ ከሙያቸው ጋር በተያያዙ ሥራዎች በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭም ሠርተዋል፡፡ ዛሬም ሥራ ላይ ናቸው፡፡