Skip to main content
x

የአፍሪካ አገሮች ለወጣቶች ፍትሐዊ የመሬት ሥርጭትን የሚከተል ሥርዓት እንዲዘረጉ ተጠየቁ

የቀድሞው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኢኒሺዬቲቭ በአሁኑ አጠራሩ የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ማዕከል የተሰኘው ተቋም፣ ከኅዳር 4 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት በሚቆየውና በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ስብሰባ የታደሙ ባለሙያዎች ወጣቶችን አሳታፊ የሚያደርግ ፍትሐዊ የመሬት ፖሊሲ በአፍሪካ እንዲተገበር ጠይቀዋል፡፡

ሉሲና ቡና ኢንሹራንስ ከፍተኛ የጉዳት ካሳ ክፍያ ማስተናዳቸውን አስታወቁ

የመድን ኢንዱስትሪውን ዘግይተው ከተቀላቀሉት ድርጅቶች መካከል ሉሲና የቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ኩባንያዎች 2009 ዓ.ም. ፈተና የበዛበትና ከፍተኛ የካሳ ክፍያ ጥያቄ ያስተናገዱበት ዓመት እንደነበር ገለጹ፡፡ የሞተር ኢንሹራንስ የካሳ ክፍያ ከዕቅዳቸው በላይ ወጪ እንደጠየቃቸውም አስታውቀዋል፡፡

አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ የተጣራ ትርፉ አምስት በመቶ ማደጉን ገለጸ

የተመላሸ ብድር የ1.7 በመቶ መጠን አስመዝግቧል አዲስ ኢንተርናሽናል ባንከ በ2009 ዓ.ም. ከታክስ በፊት ያገኘው ትርፍ ከካቻምናው የአራት ሚሊዮን ብር ብቻ ብልጫ ሲያሳይ፣ የተጣራ ትርፉ ያደገው በ4.8 በመቶ መሆኑን ገለጸ፡፡ ባንኩ ቅዳሜ፣ ኅዳር 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ወቅት ያቀረበው ሪፖርት ከታክስ በፊት 118.1 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አሳይቷል፡፡ ካቻምና የ112.8 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ የሚታወስ ሲሆን፣ በ2009 ዓ.ም.  ከታክስ በኋላ ያስመዘገበው ትርፍ ደግሞ 92.3 ሚሊዮን ብር ነበር፡፡

ብሔራዊ ባንክ ከ50 ግራም ጀምሮ ወርቅ እንዲገዛ ተወሰነ

የወርቅ ኮንትሮባንድ ንግድን ለማስቀረትና አምራቾችን ተጠቃሚ ለማድረግ፣ ብሔራዊ ባንክ ከ50 ግራም ወርቅ አንስቶ ግዥ እንዲፈጽም መንግሥት ወሰነ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሚቀርብለትን ወርቅ በአንድ ወር ውስጥ ከፍተኛ በሆነው የዓለም የወርቅ ዋጋ እንዲገዛ መወሰኑን የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሕገወጥ ንግድን ለመግታት ዕርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ የተንሰራፋውን ሕገወጥ ንግድ ለመግታት አዳዲስ ሥልቶች እንደቀየሰና በተለይ በሰባት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ዕርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በንግድ ቢሮ ላይ ባካሄደው ጥናት፣ በተለይ በሦስት ዘርፎች የሚገኙ ሰባት ችግሮችን ነቅሶ አውጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና ያነገሣቸው ተወዳዳሪዎች

በአሜሪካ ሳን ፍራንሲስኮ ከተማ መገኛውን ያደረገው ጉድ ፉድ ፋውንዴሽን የተሰኘ ተቋም፣ በየዓመቱ በምግብና ምግብ ነክ በሆኑ ምርቶች መስክ ውድድር ያዘጋጃል፡፡ ከሚያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ ውድድሮች መካከል፣ ‹‹ጉድ ፉድ አዋርድስ›› የተባለውና በምግብና መጠጦች ዙሪያ የሚሰናዳው ይገኝበታል፡፡

ከውጭ የሚመጡ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ተከታትሎ ለውጤት የማድረስ ችግሮች እንዳሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ

በተለያዩ የንግድና የኢንቨስትመንት ፎረሞች ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የንግድ ልዑካንን ተከታትሎ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረጉ ላይ ክፍተት እንደሚታይ ተገለጸ፡፡ በአገሪቱ የሚካሄዱ የቢዝነስና የኢንቨስትመንት ምክክር መድረኮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ ቢመጣም፣ ፍሬያማነታቸውን እስከ መጨረሻው በመከታተል ለውጤት ማብቃቱ ላይ ብዙ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተጠቅሷል፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ 34 የቢዝነስ ፎረሞች ተካሒደዋል፡፡

የናይል ኢንሹራንስ ካፒታል ከእጥፍ በላይ እንዲያድግ ባለአክሲዮኖች ወሰኑ

የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪውን ከተቀላቀለ 23ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ ባለአክሲዮኖች የኩባንያውን ካፒታል ወደ ግማሽ ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰኑ፡፡ ኩባንያው ሐሙስ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሄደው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ወቅት፣ የኩባንያው ዳይሬክተሮች ቦርድ ባቀረበው ሐሳብ መሠረት በአሁኑ ወቅት የተፈቀደ ካፒታሉ 200 ሚሊዮን ብር የሆነው ናይል ኢንሹራንስ፣ ካፒታሉን ከእጥፍ በላይ በማሳደግ ወደ 500 ሚሊዮን ብር ለማድረስ ስምምነት ተደርጓል፡፡

ምርት ገበያው በአንድ ወር ውስጥ ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ፈጸመ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ብቻ ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው 37,222 ቶን ያስመዘገቡ የግብርና ምርቶችን በማገበያየት ከመስከረም ወር ይልቅ ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ግብይት ማስፈጸሙን ገለጸ፡፡

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ራያ ቢራን ለመጠቅለል ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ አቀረበ

በአገሪቱ የቢራ ገበያ ከተቀላቀለ አምስተኛ ዓመቱን የያዘው የራያ ቢራ አክሲዮን ማኅበር ከፍተኛ ባለድርሻ የሆነው ቢጂአይ ኢትዮጵያ፣ ራያ ቢራን ሙሉ ለሙሉ ለመጠቅለል ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ በማቅረብ እየተደራደረ መሆኑ ታወቀ፡፡